ስለ ቶራ ጥምረት ካምፓኒ
ስለ እኛ
ቶራ ሆልዲንግ ካምፓኒ በ2012 ዓ.ም በፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ እንዲመሰረት ታስቦ የነበረ ቢሆንም በትግራይ በተከሰተው አለም አቀፍ የኮሮና ወረረሺኝና ፖለቲካዊ ችግር የታሰበውን ወደ ተግባር ሳይቀየር ቀርቷል። ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ግን ተጀምሮ የነበረው ሐሳብ በመከለስ ሚያዚያ 23/2015 ዓ/ም ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ በግልፅ ስራውን ጀምሯል። ይህ ኩባንያ ዋናው ስራው አስተዳደራዊ ስራዎች ሲሆን በኩባንያው ሥር 6 ድርጅቶች ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው የመጀመሪያ የኩባንያው መስራቾች ሆነዋል።
ሆልዲንግ ኩባንያ ለመመስረት ያስፈለገበት ምክንያት
በ2009 ዓ/ም ተመስርቶ ሰፋፊ ስራዎች ይሰራ የነበረው አንድል ንግድና ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር በኢምፖርት ኤክስፖርት፣ ሆቴል፣ እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች ተሰማርቶ እየሰራ የቆየ ድርጅት ሲሆን በሂደት መልካም የሚባል እድገት እያመጣ የነበረ ቢሆንም እንደሚፈለገው ግን አልነበረም። ምክንያቱም ድርጅቱ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን ዘርፎቹ የየራሳቸው አስተዳደርና እቅድ ስላልነበራቸው መደበላለቅና ዘገምተኛ የሆነ ለውጥና ሌሎች ችግሮች መታየት ጀመሩ።
ችግሩን የተረዱ የድርጅቱ ባለቤቶችና አመራር አቅፎ ይዟቸው የነበረው ዘርፎች ወደ 6 በመበታተንና ሌሎች አዳዲስ ስድስት ድርጅቶች እንዲመሰረቱ በማድረግ እነዚህን አቅፎ ማስተዳደር የሚችል የሆልዲንግ (ጥምረት) ድርጅት ስለሆነ ቶራ ሆልዲንግ ኩባንያ የሚል ኩባንያ እንዲቋቋም ውሳኔ ላይ ተደርሷል። ድርጅቱ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዋና ፅሕፈት ቤቱ ያደረገ ድርጅት ሲሆን ለትግራይ የመጀመሪያ ሆልዲንግ ኩባንያ ነው።
ቶራ ማለት ምን ማለት ነው
ቶራ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ኦሪት/ቃል/ ማለት ነው።
በተጨማሪም ቶራ የሚባል እንስሳ በዛ ያለ ቀንድ/ቀንዱ ባለ ብዙ ቅርንጫፍ/ ያለው እንስሳ ማለት ነው።
ይህ ከትግርኛ ወደ አማርኛ በትክክል መተርጎሜን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 205 በቃለ መሃላ አረጋግጣለሁ።
ኩባንያችን ደግሞ ተጠቃሚዎቹን በማንኛውም ወቅት በቃሉ መሰረት የሚገኝና ተጠቃሚዎቹ በየምርጫቸው ሊስተናገዱበት የሚችሉ አሰራር በመዘርጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ አቅዶ የሚንቀሳቀስ ኩባንያ ነው። በመሆኑም ይህ ስም ስለሚገልፀው ኩባንያችን ይህንን ስያሜ መጠቀም ችሏል።
ተልእኮ
በትላልቅ ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሳተፍ ዓለም የደረሰበት ቴክኖሎጂ በመያዝ ለአገራችን ብሎም የዓለም ህዝቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጥራትና ታማኝነት ያለው አገልግሎት በመስጠት በከፍተኛ ደረጃ መድረስ ነው።
የድርጅታችን የጋራ እሴቶች
- የላቀ ቴክኖሎጂ ባለቤትነት
- ቅንነት
- ውጤታማነት
- ጥራትና ተመራጭነት
- መፍትሔ ሰጪነት
- የሠራተኞች እድገትና ልማት
- መሪነት
- ድርጅታዊ ጥምረት
- ማህበራዊ ኃላፊነት
- መተጋገዝና መደጋገፍ
አላማ
በተጠቃሚዎቻችን ቅቡልነት ያገኘ ግልፅና ታማኝ የሆነ ጥምረት (አንድነት) ሕብረት በሚያጠናክር ተፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ የድርጅታችን ጥቅም መጠበቅና ማስተዳደር
አመራር
ከአማኑኤል ጋር ተዋወቁ፤ የበለጸገ ኩባንያ ፕሬዚዳንትና ባለቤት በመሆን ሁለት ባርኔጣዎችን የሚለብስ ታታሪ ግለሰብ። አማኑኤል እያንዳንዱ ውሳኔ ከላይ ከተቀመጡት ግቦቹ ጋር እንዲስማማ በማድረግ በራእይ አስተሳሰብና በአመራር ችሎታ ኩባንያውን ወደ ስኬት ይመራዋል ። እንደ ፕሬዘደንት፣ ቡድኑ ለጥሩነት እና ለአዳዲስ ነገሮች ጥረት እንዲያደርግ በማነሳሳት ምሳሌ በመሆን ይመራል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ባለቤቱ የአማኑኤል የድርጅት መንፈስ ለእድገትና ለመስፋፋት ያለማቋረጥ እድል እንዲፈልግ ይገፋፋዋል፣
Amanuel Nrayo (President and Owner)
ለምን ምረጡን
benefit 1
A short description of the benefit.
benefit 2
A short description of the benefit.
benefit 3
A short description of the benefit.
benefit 4
A short description of the benefit.